ከዛሬ አምስት ወይም ስድስት አመት በፊት ይመስለኛል ሀይሌ ገብረስላሴ እና ሌሎች አትሌቶች ለአንድ የስፖርት ዝግጅት አሰላ ተገኝተው ነበር፡፡ በዚህም ወቅት ሁሉም ለማለት ይቻላል በነበረው ሙቀት በጣም ተገርመዋል፡፡ ያ የሚያውቁትና ያደጉበት አካባቢ በዚህ ደረጃ ተለውጦ ሞቃታማ መሆኑ ብዙ አነጋግሯቸዋል፡፡ በእርግጥ ወቅቱ በጋ ነበር፣ ቢሆንም በከፍተኛ አልቲትዩድና በደጋ አየር ጠባዩዋ የሚያውቋት ከተማ ሸሚዝ አስወላቂ መሆኗ አስደንቋቸዋል፡፡ እሩቅ ሳይኬድ አዲስ አበባ ቀበና ወንዝ ሲዋኙ ያደጉ ልጆች አሁን ትልቅ ሰው ሆነው ሲያዩት ቀበና “ወንዝ የነበረ” እንጂ አሁንስ ወንዝ እንዳይደለ በቅሬታና መገረም ይናገራሉ፡፡ ይህን ሁሉ የምንለው የአለማያን ሐይቅ መድረቅ ሳናነሳ ነው፡፡ አለም እየሞቀች ነው፣ ወትሮ በቀላሉ ያልፉ የነበሩ ከአትላንቲክ እና ሰላማዊ ውቅያኖስ ዳርቻ የሚነሱ ማዕበሎችና…
Author: Taye Mohammed
ግሪጎርያን የዘመን አቆጣጠር የሚባለው የአቆጣጠር ስያሜ ዘይቤውን በወሰኑት ጳጳስ በአቡን ግሪጎሪ ስምንተኛ ስም የተሰየመ ነው፡፡ የግሪጎርያን ዘመን አቆጣጠር በጸኃይ ቀን አቆጣጠር ላይ የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአለም በስፋት የሚሰራበት ነው፡፡ ጃንዋሪ የአዲስ አመት መግቢያ የሆነው የሮማውያንን ‘’የጅማሮ አምላክ’’ (ጎድ ኦፍ ቢግኒንግስ) ጃኑስ ለመዘከር፣ በዚያው ስም በሚጠራው የአዲስ አመት መግቢያ ወር እንዲሆን በ 1582 በያኔው የሮማ ጳጳስ ግሪጎሪ ስምንተኛ ውሳኔ ነው፡፡ይህም ማለት ጃንዋሪ የአመቱ መጀመረያ ወር ከሆነ፣ ጃንዋሪ አንድ የግድ የአመቱ መጀመርያ ቀን ይሆናል፡፡ በኃላ ግን በመካከለኛ ዘመን ክርስትያኖች የአመቱን መጀመርያ ቀን ሀይማኖታዊ ይዘት ባለው ቀን ለመቀየር ሙከራዎች ተደርገው ነበር፡፡ሆኖም በሂደት ብዙ ሀገራት ይህን የዘመን አቆጣጠር መከተል ጀመሩ፡፡የተለያዩት የጣልያን ግዛቶች፣ ስፔይን፣…