Author: Taye Mohammed

የስንክሳር በይነ-መረብ ወርሀዊ መጽሄት የጠቅላላ ዕውቀት መንሸራሸሪያ መጽሄት ስትሆን በውስጧም አለም-አቀፍ ግንኙነቶች፣ባህልና ስነ- ጥበብ፣ታሪክ፣አሰሳ፣ከመጽሐፍት ሰፈር፣ ሳይንስ፣ እና አካባቢ ጥበቃን የሚመለከቱ መጣጥፎች ይቀርቡባታል፡፡የመጽሄቷ ተልዕኮ አለም-አቀፍ ግንኙነቶች፣ ባህልና ስነጥበብ፣ ታሪክ፣አሰሳ፣ ከመጽሐፍት ሰፈር፣ሳይንስ፣እና አካባቢ ጥበቃን ርዕስ ያደረጉ መጣጥፎችን በማቅረብ በተማሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በከፊል የሚንጸባረቀውን የጠቅላላ እውቀት ጥማት ለማርካት የራሳችንን እና የሌሎችን አስተዋጽዖ አጣምሮ ማበርከት ነው፡፡የመጽሄቷ ራዕይ መጽሄቷን በ 2030 ከላይ በጠቀስናቸው ርዕሶች አሉ የተባሉ ልሂቃን የሚጽፉባት፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቀለም ቀመስ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤትና በዲያስፖራ የመጽሄቷ ቋሚ ተከታታይ የሚሆኑባት፣ በነዋይ ረገድም ዳብራ ሀገር-በቀል ጠቀሜታ ያላቸው በአመት ከአራት ያላነሱ የምርምርና ጥናት ጽሁፎች የሚቀርቡባት ተወዳጅ የበይነ መረብና እንዲሁም የህትመት መጽሄት ማድረግ ነው፡፡የመጽሄቷ ግብ የሚቀርቡት መጣጥፎች…

Read More

(ትንሿ ሜትሮፖሊታን – አዋሽ 7 ኪሎ) ክፍል አንድ ያለፈው አልፎ አልፏልናዳግም ላይመለስ ሄዷልናእንደ ጥንቱ መሆን ቀርቷልናዛሬ ሌላ ሆኖ ቀርቧልና (ግጥም ተስፋዬ ለማ፣ ዘፋኝ ጥላሁን ገሠሠ) የልጅነት እድገታችን በአዋሽ ሰባት ኪሎ – የቅድመ-ፌዴላሪዝም ትውስታ በስንክሳር አይን ስንመለከተው እድገታችን በአዋሽ ሰባት ኪሎ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ ሰይድ ሰቃፍእስቲ ትንሽ ስለ ሰይድ ሰቃፍ እናውራ፡፡ ሲጀመር ሰይድ ሰቃፍ ትክክለኛ ስማቸው ሰቃፍ ዑመር ነው፡፡ ነገር ግን ዝርያቸው ከነቢዩ መሐመድ ሰለሚቆጠር ‘‘ሰይድ‘’ የሚባለው ማዕርግ ስለሚሰጣቸው ነው ሰይድ ሰቃፍ እያልን የምንጠራቸው፡፡ የነቢዩ መሐመድ ዝርያዎች ቁርያሽ ከሚባል ጎሳ ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን የኛዎቹ አረቦች የየመን ዝርያ በተለይም ሀድረሞት ከተባለ አቢይ ጎሳ ፈልቀው ዘቅሩሪ፤ሸቡጢ እና በመሳሰሉት ንዑስ ጎሳዎች የተከፋፈሉ በብዛት፣ሰቃፍ…

Read More

(ትንሿ ሜትሮፖሊታን – አዋሽ 7 ኪሎ) ክፍል አንድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የነበረው ኃይሉ ጎሹ የአዋሽ ምድር ባቡር ፖሊስ ሆኖ ከአንድ ጊዜ በላይ ለአዋሽ ምድር ባቡር ክበብ ተጫውቷል፡፡ እርግጥ ጨዋታው መጋላ እና ባቡር ተብሎ ይደረግ የነበረ የትንሽ ከተማ ጨዋታ ነው ፤ግን ተጫውቷል፡፡ ለልምምድ ከለገሀሩ ስልከኛ ከደመረው ጋር ኳስ እየተቀባበሉ ሲጫወቱ ልጅም ብሆን ትዝ ይለኛል፡፡ አቀንቃኙ አሊ መሐመድ ቢራም በአዋሽ 7 ኪሎ ለገሀር ቦምብዬ (የውኃ ክፍል) ሰራተኛ ነበር፡፡ የሽቦ ጊታር ነበረችውና በዚያች በኃላ ዝነኛ የሆነባቸውን ዜማዎች ሲያንጎራጉር አውቃለሁ፡፡ በጊዜው የከተማው ትልቅ ሰው ግራዝማች ሰይድ አሊ ልጃቸውን አቡበከርን ሲድሩ በሰፊው ሰርገው ነበር፡፡ ከአዋሽ በስራ እና በትምህርት እስከወጣንበት ጊዜ ድረስ እንደዚያ አይነት ሰርግ…

Read More

በቅርቡ ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሆኖ ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጧል፡፡ በሚቀጥለው ጃንዋሪ 20 2025 ኋይት ሐውስ ገብቶ ስራውን ይጀምራል፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ በ 2016 ሂለሪ ክሊንተንን አሸንፎ ስልጣን ሲይዝ በአሜሪካና በተለይም በተቀረው አለም ትልቅ መረገምና ፍርሀትን ፈጥሮ ነበር፡፡ አሁን፣ መገረሙ ቢቀንስም በሱ ስልጣን መያዝ ፍርሀትና ሀዘን በብዙ የአለም ክፍሎች ተከስቷል፡፡ አውሮፓውያን፣ ትራምፕ ኔቶን ቢያንስ ያዳክማል ሲከፋም ጥሎ ይወጣል ብለው በእጅጉ ሰግተዋል፡፡ ቻይኖች ከፍተኛ የንግድ ታሪፍ ይጥልብናል ብለው አንቅልፍ አጥተዋል፡፡ ጃፓንና ደቡብ ኮርያ በየአገሮቻቸው ላሉት የአሜሪካ ጦር ሰፈር ወጪ ጠቀም ያለ ገንዘብ መድቡ ይለናል ብለው ፈርተዋል፡፡ በተለያዩ አምባገነን መሪዎች ስር ያለው የኤሽያ እና አፍሪካ ህዝብ ትራምፕ የአምባገነኖች አድናቂ እና በተለይ ስለ አፍሪካ…

Read More

መንደርደሪያ በልጅነቴ አዋሽ 7ኪሎ የሰብለወንጌል አንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ዳይሬክተራችን አቶ ፀጋዬ፣ በጠዋቱ የባንዲራ ማውጣት ሰልፍ ላይ ዛሬ ከቀትር በፊት ትምሕርት እንደሌለ ነገረን፡፡ ምክንያቱ ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰዐት ጀምሮ እስከ ስድስት ሰዐት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግና ተማሪዎችም በብሄራዊ በዐላት እንደምናደርገው በስነ-ስርዐት ተሰልፈን ሰላማዊ ሰልፉን እንደምናደምቅ ነገረን፡፡ ለካ ትናንትና (ሰኞ) መምህራኑ እና ትልልቆቹ ተማሪዎች ለሰልፉ ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር፡፡ በእንጨት ላይ በጨርቅ የተጻፉ መፈክሮች ሲያዘጋጁ፡፡ በዚያኑ ሰሞን አንድ ይሁን ሁለት አሁን ተዘንግቶኛል የኢትዮጵያ አየርመንገድ አውሮፕላኖች ተጠልፈው ነበር፡፡ እና በሬድዮ እንደሰማነው፣ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ የሚሰሩ፣ በአንዳንድ የአረብ ሐገራት የተገዙ፣ ‘’ኤርትራን ከእናት ሀገሯ አስገንጥለው ቀይ ባሕርን የአረብ ሐይቅ ለማድረግ የሚታገሉ…

Read More

ከዛሬ አምስት ወይም ስድስት አመት  በፊት ይመስለኛል ሀይሌ ገብረስላሴ እና ሌሎች አትሌቶች ለአንድ የስፖርት ዝግጅት አሰላ ተገኝተው ነበር፡፡ በዚህም ወቅት ሁሉም ለማለት ይቻላል በነበረው ሙቀት በጣም ተገርመዋል፡፡ ያ የሚያውቁትና ያደጉበት አካባቢ በዚህ ደረጃ ተለውጦ ሞቃታማ መሆኑ ብዙ አነጋግሯቸዋል፡፡ በእርግጥ ወቅቱ በጋ ነበር፣ ቢሆንም በከፍተኛ አልቲትዩድና በደጋ አየር ጠባዩዋ የሚያውቋት ከተማ ሸሚዝ አስወላቂ መሆኗ አስደንቋቸዋል፡፡ እሩቅ ሳይኬድ አዲስ አበባ ቀበና ወንዝ ሲዋኙ ያደጉ ልጆች አሁን ትልቅ ሰው ሆነው ሲያዩት ቀበና “ወንዝ የነበረ” እንጂ አሁንስ ወንዝ እንዳይደለ በቅሬታና መገረም ይናገራሉ፡፡ ይህን ሁሉ የምንለው የአለማያን ሐይቅ መድረቅ ሳናነሳ ነው፡፡ አለም እየሞቀች ነው፣ ወትሮ በቀላሉ ያልፉ የነበሩ ከአትላንቲክ እና ሰላማዊ ውቅያኖስ ዳርቻ የሚነሱ ማዕበሎችና…

Read More

ግሪጎርያን የዘመን አቆጣጠር የሚባለው የአቆጣጠር ስያሜ ዘይቤውን በወሰኑት ጳጳስ በአቡን ግሪጎሪ ስምንተኛ ስም የተሰየመ ነው፡፡ የግሪጎርያን ዘመን አቆጣጠር በጸኃይ ቀን አቆጣጠር ላይ የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአለም በስፋት የሚሰራበት ነው፡፡ ጃንዋሪ የአዲስ አመት መግቢያ የሆነው የሮማውያንን ‘’የጅማሮ አምላክ’’ (ጎድ ኦፍ ቢግኒንግስ) ጃኑስ ለመዘከር፣ በዚያው ስም በሚጠራው የአዲስ አመት መግቢያ ወር እንዲሆን በ 1582 በያኔው የሮማ ጳጳስ ግሪጎሪ ስምንተኛ ውሳኔ ነው፡፡ይህም ማለት ጃንዋሪ የአመቱ መጀመረያ ወር ከሆነ፣ ጃንዋሪ አንድ የግድ የአመቱ መጀመርያ ቀን ይሆናል፡፡ በኃላ ግን በመካከለኛ ዘመን ክርስትያኖች የአመቱን መጀመርያ ቀን ሀይማኖታዊ ይዘት ባለው ቀን ለመቀየር ሙከራዎች ተደርገው ነበር፡፡ ሆኖም በሂደት ብዙ ሀገራት ይህን የዘመን አቆጣጠር መከተል ጀመሩ፡፡ የተለያዩት የጣልያን…

Read More