ያለፈው የአውሮፓውያን አመት ብዙ የተፈጥሮ አደጋዎች የተስተናገዱበት አመት ነው፡፡ እዚህ አጠገባችን ስፔይን በጎርፍ አደጋ የደረሰውን ጥፋት አይተናል፡፡ ኢትዮጵያም ምድሪቱ እየንቀጠቀጠች ታስፈራራናለች፡፡ አመቱ ሲገባደድ ደግመን ደጋግመን የሰማነው የአየር ንብረት ዜና ምድራችን እንደ አምና ጨርሶ ሞቃ እንደማታውቅ ነው፡፡ በዚች አጭር መጣጥፍ በ 2024 በአለማችን የተከሰቱትን ዋና የተፈጥሮ አደጋዎችን እና ለአደጋዎቹ መክፋት የከባቢ አየር ለውጥ ያለውን ድርሻ ለመቃኘት እንሞክራለን፡፡ የኬራላ ግዛት ሀገር ጎብኝዎች ከሚያዘወትሯቸው ቦታዎች አንዷ ስትሆን በሕንድ ደቡብ ጠረፍ ትገኛለች፡፡ ኦገስት 20/2024ጠዋት በዌያናድ ወረዳ ኮረብታዎች ሲጥል በቆየው ከባድ ዝናብ ላይ ከባድ የመሬት መናድ ፈጥሯል፡፡ በዚህም ሳቢያ የቀዬው ነዋሪዎች በመኝታቸው እንዳሉ ውኃ፣ ጭቃና፣ቋጥኝ ተደርምሶባቸው ሞተዋል፡፡ በአደጋው 205 ሰዎች ሲሞቱ 200ው ደሞ ጠፍተዋል፡፡ (REUTERS)…
Author: Taye Mohammed
ከአንድ አመት ከሶስት ወር በፊት ያኔ ጋዛን የሚያስተዳድረው የሀማስ ቡድን በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና አስደናቂ ጥቃት ፈጸመ፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመበት እለት የጥቃቱን ያህል አስገራሚ እና ታሪካዊ ነበር፡፡ ኦክቶበር 7 ቀን 2023 ልክ በዚህን እለት ማለት ኦክቶበር ሰባት 1967 ዓ.ም ግብጽ እና ሶርያ በ 1967 ዓ.ም በእስራኤል የተወሰዱባቸውን የጎላን ኮረብታ እና የሲናን ምድር ለማስመለስ ድንገታዊ ጥቃት በእስራኤል ላይ የከፈቱበት ቀን ነው፡፡ ያንን ጥቃት ተከትሎ የ17ቱ ቀን የእስራኤልና አረቦች አራተኛው ዙር ጦርነት ተካሄደ፡፡ ልክ ከ 57 አመት በኃላ ሀማስ እስራኤል ሳትዘጋጅ እና ሳትጠብቀው ኦክቶበር 7ቀን 2024 ጥቃት አካሄደባት፡፡ በዚህም ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ የሀማስ ተዋጊዎች ሮኬቶችን፣ እና ድሮኖችን በመጠቀም ጥቃት ፈጸሙ፡፡ በዚህም ጥቃት‘’ከ 1200…
ልጅ ሆነን ሀብት የእግዜር ስጦታ እንደሆነ ነበር የሚነገረን፡፡ በል ካለው አምላክ እማትሸከመውን አዱኛ ይሰጥሀል፣ በፀሎት መበርታት ብቻ ነው ዋናው፡፡ ታድያ እንዲያ የሚመስለን ልጆቹን ብቻ አልነበረም አዋቂዎቹን ጭምር እንጂ፡፡ አዋሽ ሰባት ኪሎ ለገሀር ከዋናው ቢሮ በስተግራ መኪና እህል የሚያራግፍበት ሰፊ የሲሚንቶ በረንዳ ነበር፡፡ ከሰዐት ከ10 ተኩል በኃላ ጸኃዩዋ በረድ ስትል የለገር ሀማሎች ተቀምጠው ጫታቸውን ይቅማሉ፡፡ በመሀል ከከተማዋ የመጣ አንድ ደረሳ (የሙስሊም ዲያቆን) ተቀላቅሎአቸው እየቃመ፣ሙስባሐውን እየቆጠረ አላህን ይለማመናል፡፡ “ያ አላህ ኧረ በ ርዝቅህ (ድንገተኛ ሐብት) አትርሳኝ፡፡ አሁን በረካህን አንዴ ብታዘንብብኝ ምን ይጎልብሀል? ያ አላህ በል እንጂ!”በማለት ሁለት እጆቹን ከፍቶ ወደ ሰማይ እያየ ይጸልያል፡፡ምንም ጠብ አላለም፣ “እንዴ አትርሳኝ እንጂ!” ምንም የለም “አቦ ርዝቅ…
እንግዲህ ጊዜው ስለረዘመ ትክክለኛ ቀኑን አላስታውሰውም ብቻ በሰብተምበር ውስጥ 1989 የአንድ ጓደኛዬ እናት ስላረፉ ለቅሶ ለመድረስ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ወደሚገኝበት መርቲ ከተማ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ነገሩን የሰማሁት አርብ ሲሆን ቅዳሜ ጠዋትን እረፍት ወስጄ እሑድ ለመምጣት በማሰብ አርብ እለት ለፈቃድ ከሰዐት አለቃዬ ቢሮ ሄድኩ፡፡ አለቃዬ አንድ የኒውስዊክ መጽሄት እያገላበጠ ሲመለከት ደረስኩኝ፡፡ የመጣሁበትን አስረድቼ አዎንታዊ መልስ ከተቀበልኩ በኃላ ወዲያው ከመውጣት ትንሽ ሌሎች ጉዳዮችን አንስቶ መነጋገሩ የጨዋ ደንብ ስለመሰለኝ ስለሚያነበው መጽሄት ጠየቅሁት፡፡ ‘’ከጌታቸው ተውሼ እያየሁት ነበር፣ እንካ ዋና ዋና ነገሩን ማየት ከፈለግህ፣የተዋስኩት ትናንት ስለሆነ በኃላ እመልስለታለሁ’’ ብሎ መጽሄቱን አቀበለኝ፡፡ የፊት ሽፋኑ ላይ በውሃ ሰማያዊ መደብ ላይ አንድ ደማቅ ሰማያዊ ነገር ፣መሀሏ ላይ አንድ ትልቅ…
ቀኑ ደርሶ ዶናልድ ትራምፕ ኋይት ሐውስ ግብቶ ስራውን ጀምሯል፡፡ እስካሁን እንዲተገበሩ ያዘዛቸውም ሆነ በይፋ ይደረጋሉ ብሎ የወሰናቸውን ነገሮች አስቀምጧል፡፡ አንዳንዶቹ የተጠበቁም ቢሆኑ ለአሜሪካም ሆነ አለም የማይበጁ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ጭራሹኑ በጊዜ ሂደት ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለፍጥረታት በአጠቃላይ አጥፊነት ያላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ በከባቢ አየር ጥበቃ ላይ የወሰዳቸውና ለመተግበር በአጀንዳ የተያዙት፡፡ በዚህ መጣጥፍ ሁሉንም የፕሬዚዳንቱን ውሳኔዎች ሳይሆን፣በሲመተ በአሉ ላይም ሆነ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ሲናገራቸውና በፊርማውም ሲደነግጋቸው ከነበሩት ውስጥ ትኩረታችን የሳቡትን ሁለቱን ብቻ እናቀርባለን ፕሬዚዳንቱ ትዕዛዛቱን እየፈረሙ መጀመርያ ስለ ስደተኞች መቸም የትራምፕ ነገር በስመ አቡ ‘’ስደተኛ’’ ነው፡፡ እሱ ራሱ ታድያ የስደተኞች የልጅ ልጅ ነው፡፡ ስለ ትራምፕ ስደተኛ ወላጆች በመጣጥፉ መጨረሻ ላይ እንመለስበታለን፡፡ ለአሁኑ…
(ትንሿ ሜትሮፖሊታን – አዋሽ 7 ኪሎ) ክፍል ሁለት ደብረሳሌም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ይህች ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ ያሰሯት ቤተክርስትያን (ቤ/ክ) ከህይወቴ አራቱን አመት ያሳለፍኩባት ነች፣ በቄስ ተማሪነት፡፡ በቅጥር ግቢው ያለውን የመቃብር ስፍራ የባረኩት በኃላ ፓትርያክ የሆኑት አቡነ ባስልዮስ ሲሆኑ በዚህም ምክንያት እዚያ መቀበር የሚፈቀድላቸው የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ነበሩ፡፡ እንደመታደል ሆኖ ከነዚህ አንዷ እናቴ ሙላቷ እንግዳወርቅ ምንዋልኩለት ትገኛለች፡፡ የአዋሽ ቤ/ክ በጣልያን ጊዜ ጽላቱ ተደብቆ ጫካ ውስጥ ሲኖር መምሬ ማሞ አብረው በሳቢል ጓሮ ገደል ተደብቀው ይጠብቁትና ይንከባከቡት ነበር፡፡ በዚህ ረገድ በድብቅ የሚረዷቸው ግለሰብ ነበሩ፡፡ እኚህ ግለሰብ በእምነት ሙስሊም ቢሆኑም የክርስትያኖቹን ችግር አይተው እርዳታቸውን ከመስጠት አልተገቱም፡፡ መምሬ ማሞ በድብቅ የቤ/ክርስትያኑን አልባሳት ከተማ ያመጡና…
የስንክሳር በይነ-መረብ ወርሀዊ መጽሄት የጠቅላላ ዕውቀት መንሸራሸሪያ መጽሄት ስትሆን በውስጧም አለም-አቀፍ ግንኙነቶች፣ባህልና ስነ- ጥበብ፣ታሪክ፣አሰሳ፣ከመጽሐፍት ሰፈር፣ ሳይንስ፣ እና አካባቢ ጥበቃን የሚመለከቱ መጣጥፎች ይቀርቡባታል፡፡የመጽሄቷ ተልዕኮ አለም-አቀፍ ግንኙነቶች፣ ባህልና ስነጥበብ፣ ታሪክ፣አሰሳ፣ ከመጽሐፍት ሰፈር፣ሳይንስ፣እና አካባቢ ጥበቃን ርዕስ ያደረጉ መጣጥፎችን በማቅረብ በተማሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በከፊል የሚንጸባረቀውን የጠቅላላ እውቀት ጥማት ለማርካት የራሳችንን እና የሌሎችን አስተዋጽዖ አጣምሮ ማበርከት ነው፡፡የመጽሄቷ ራዕይ መጽሄቷን በ 2030 ከላይ በጠቀስናቸው ርዕሶች አሉ የተባሉ ልሂቃን የሚጽፉባት፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቀለም ቀመስ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤትና በዲያስፖራ የመጽሄቷ ቋሚ ተከታታይ የሚሆኑባት፣ በነዋይ ረገድም ዳብራ ሀገር-በቀል ጠቀሜታ ያላቸው በአመት ከአራት ያላነሱ የምርምርና ጥናት ጽሁፎች የሚቀርቡባት ተወዳጅ የበይነ መረብና እንዲሁም የህትመት መጽሄት ማድረግ ነው፡፡የመጽሄቷ ግብ የሚቀርቡት መጣጥፎች…
(ትንሿ ሜትሮፖሊታን – አዋሽ 7 ኪሎ) ክፍል አንድ ያለፈው አልፎ አልፏልናዳግም ላይመለስ ሄዷልናእንደ ጥንቱ መሆን ቀርቷልናዛሬ ሌላ ሆኖ ቀርቧልና (ግጥም ተስፋዬ ለማ፣ ዘፋኝ ጥላሁን ገሠሠ) የልጅነት እድገታችን በአዋሽ ሰባት ኪሎ – የቅድመ-ፌዴላሪዝም ትውስታ በስንክሳር አይን ስንመለከተው እድገታችን በአዋሽ ሰባት ኪሎ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ ሰይድ ሰቃፍእስቲ ትንሽ ስለ ሰይድ ሰቃፍ እናውራ፡፡ ሲጀመር ሰይድ ሰቃፍ ትክክለኛ ስማቸው ሰቃፍ ዑመር ነው፡፡ ነገር ግን ዝርያቸው ከነቢዩ መሐመድ ሰለሚቆጠር ‘‘ሰይድ‘’ የሚባለው ማዕርግ ስለሚሰጣቸው ነው ሰይድ ሰቃፍ እያልን የምንጠራቸው፡፡ የነቢዩ መሐመድ ዝርያዎች ቁርያሽ ከሚባል ጎሳ ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን የኛዎቹ አረቦች የየመን ዝርያ በተለይም ሀድረሞት ከተባለ አቢይ ጎሳ ፈልቀው ዘቅሩሪ፤ሸቡጢ እና በመሳሰሉት ንዑስ ጎሳዎች የተከፋፈሉ በብዛት፣ሰቃፍ…
(ትንሿ ሜትሮፖሊታን – አዋሽ 7 ኪሎ) ክፍል አንድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የነበረው ኃይሉ ጎሹ የአዋሽ ምድር ባቡር ፖሊስ ሆኖ ከአንድ ጊዜ በላይ ለአዋሽ ምድር ባቡር ክበብ ተጫውቷል፡፡ እርግጥ ጨዋታው መጋላ እና ባቡር ተብሎ ይደረግ የነበረ የትንሽ ከተማ ጨዋታ ነው ፤ግን ተጫውቷል፡፡ ለልምምድ ከለገሀሩ ስልከኛ ከደመረው ጋር ኳስ እየተቀባበሉ ሲጫወቱ ልጅም ብሆን ትዝ ይለኛል፡፡ አቀንቃኙ አሊ መሐመድ ቢራም በአዋሽ 7 ኪሎ ለገሀር ቦምብዬ (የውኃ ክፍል) ሰራተኛ ነበር፡፡ የሽቦ ጊታር ነበረችውና በዚያች በኃላ ዝነኛ የሆነባቸውን ዜማዎች ሲያንጎራጉር አውቃለሁ፡፡ በጊዜው የከተማው ትልቅ ሰው ግራዝማች ሰይድ አሊ ልጃቸውን አቡበከርን ሲድሩ በሰፊው ሰርገው ነበር፡፡ ከአዋሽ በስራ እና በትምህርት እስከወጣንበት ጊዜ ድረስ እንደዚያ አይነት ሰርግ…
በቅርቡ ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሆኖ ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጧል፡፡ በሚቀጥለው ጃንዋሪ 20 2025 ኋይት ሐውስ ገብቶ ስራውን ይጀምራል፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ በ 2016 ሂለሪ ክሊንተንን አሸንፎ ስልጣን ሲይዝ በአሜሪካና በተለይም በተቀረው አለም ትልቅ መረገምና ፍርሀትን ፈጥሮ ነበር፡፡ አሁን፣ መገረሙ ቢቀንስም በሱ ስልጣን መያዝ ፍርሀትና ሀዘን በብዙ የአለም ክፍሎች ተከስቷል፡፡ አውሮፓውያን፣ ትራምፕ ኔቶን ቢያንስ ያዳክማል ሲከፋም ጥሎ ይወጣል ብለው በእጅጉ ሰግተዋል፡፡ ቻይኖች ከፍተኛ የንግድ ታሪፍ ይጥልብናል ብለው አንቅልፍ አጥተዋል፡፡ ጃፓንና ደቡብ ኮርያ በየአገሮቻቸው ላሉት የአሜሪካ ጦር ሰፈር ወጪ ጠቀም ያለ ገንዘብ መድቡ ይለናል ብለው ፈርተዋል፡፡ በተለያዩ አምባገነን መሪዎች ስር ያለው የኤሽያ እና አፍሪካ ህዝብ ትራምፕ የአምባገነኖች አድናቂ እና በተለይ ስለ አፍሪካ…